ስንክሳር icono

4.8.1 by Samuel Minale


21/03/2024

Acerca del ስንክሳር

Español

ስንክሳር ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Sinksar la Iglesia Ortodoxa Tewahedo en amárico e inglés

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!

ስንክሳር ማለት የእግዚአብሔርን ረድኤት አጋዥ በማድረግ በበጎ ስጦታውም የተሰበሰበ ማለት ነው።

ይህ ሃይማኖቶታቸው የቀና የከበሩ አባቶች ፣ ከቅዱሳን ሰማዕታት ፣ ከጻድቃን ፣ ከነቢያት ፣ ከሐዋርያት ፣ ከሊቃነ ጳጳሳት ፣ ከኤጲስቆጶሳት ፣ ከመነኮሳትም ሁሉ ከገዳማውያንም ከገድሎቻቸው ከመላእከት አለቆችም ከድርሳናቸው የሰበሰቡትና ያቀነባበሩት አምላክን የወለደች እመቤታችን የከበረች ድንግል ማርያም ከአደረገቻቸው ድንቆች ተአምራቶችም የክብር ባለቤት የሆነ የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የበዓላቶቹን መታሰቢያ በዘመናት ሁሉ እስከ ዓመቱ ፍፃሜ ሁል ጊዜ ምእመናን እንዲያነቡት እንዲሰሙትም ይሆን ዘንድ ተዘጋጀ።

ይህንንም ቅዱስ መጽሐፍ ሰብስበው ያቀነባበሩት በሽህ ሦስት መቶ ንጹሐን በሆኑ ሰማዕታት ዘመን ነው። የእሊህ የተባረኩ አባቶቻችን ጸሎታቸውና በረከታቸው ከእኛ ጋር ይኑር።

ለዘላለሙ አሜን !!

የቅዱሳንን ታሪክ ለማንበብ ከታሪካቸውም ለመማር እኛም በክርስትና ህይወታችን እንዲሁም በእለት ተእለት የኑሮ እንቅስቃሴያችን ውስጥ በዋነኝነት ቅዱሳኑ እንዲራዱን እንዲያማልዱንም በሌላም መልኩ ከነሱ የክርስትና ህይወት በመነሳት እኛስ ምን ማረግ እንችላለን ከቅዱሳኑ ታሪክ ምንን እማራለው የሚለውን እንድናስብ ይረዳናል ብሎ በማሰብ እንዲሁም በብዙ መፅሃፈ ስንክሳርን ማግኘት በማይችሉ ምእመናን ጥያቄ መሰረት ይህን የሞባይል እንዲሁም ከጉዋደኞቾ ፣ ቤተሰቦቾ ፣ የስራ ባልደረቦቾ ባጠቃላይ ከወዳጅ ዘመዶቾ ጋር በመሆን ይጠቀሙበት ዘንድ ትልቁን የቤተክርስቲያን መፅሃፍ መፅሃፈ ስንክሳርን ጠቅለንም ባይሆን ፈጣሪ በፈቀደ የቻልነውን ሙሉውን ታሪክ ያልቻልነውን ደግሞ ዋና ታሪኩን ጨምቀን አቅርበናል።

እርሶም እኝህን መንፈሳዊ ታሮኮች ሰአት መድበው በቀን ቢያንስ ከ3—10 ደቂቃ ወስደው የእለቱን ስንክሳር እንዲያነቡ እንዲማሩበት ከወዳጆቾ ጋርም ውይይቶችን እኒዲያረጉበት እንመክራለን።

በዚህ አፕሊኬሽን ውስጥ የተካተቱት ብዙሃኑ ቅዱሳን ከ 6 ቱ እህታማማች ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ አብያተ ክርስትያናት ናቸው

እነዚህም አብያተ-ክርስትያናት: -

- የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

- የ ግብፅ / አሌክሳንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን

- የ ሶሪያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን

- የ አርመንያ ሐዋርያዊ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን

- የ ኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

- የ ህንድ - ማንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን

ያንብቡ ያነበቡትንም ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር በመሆን ይወያዩበት - አፕሊኬሽኑንም ለሌላቸው ያካፍሉዋቸው

ድጋፍዎ አስተያየትዎ አይለየን

ፈጣሪ ከቅዱሳኑ ይደምረን

አሜን !!

በዚህ እለት ማን ቅዱስ እንደሚከብር ያውቃሉ? ከነ ታሪካቸው ገብተው ይመልከቱ ከበረከታቸውም ተካፋይ ይሁኑ። ይህንንም ስራ ሰርቶ ለማጠናቀቅ አመታትን የፈጀ ሲሆን በዚህ ስራ ላይ አብዛኞቹን ፅሁፎቹን በማዘጋጀት የላቀ ሚና ለተገበረው ለዲ / ን ዮርዳኖስ አበበ ምስጋናችን ከልብ ነው።

ዲ / ን ዮርዳኖስም ለብዙ አመታት እድሜውን ሙሉ መንፈስ ቅዱስ ባቀበለው መጠን ጎንደር በሚገኘዉ በዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ የቅዱሳን ታሪክ በመማር ፣ በማንበብ ፣ በመተርጎም ፣ በመፃፍ ፣ በማዘጋጀት እና በማስተማር ጭምር የኖረ የቤተክርስቲያናችን አገልጋይ ነው። ይህንንም እርሱ ያዘጋጃቸውን ፅሁፎች በነፃ ምዕመንን ለማስተማር በፌስ ቡክ ፣ በቴሌ ግራም እንዲሁም ለኛም በነፃ ሰጥቶን እኛም ዘመኑን በሚዋጅ መልኩ ህዝበ ክርስቲያኑን ለማስተማር እና የቅዱሳን በረከትንም ለኛም ላንባቢውም እንድንካፈል በአፕሊኬሽን መልክ አቅርበናል።

ስንክሳር * Sinksar - (Vidas de los santos) en amárico e inglés.

ስንክሳር (የቅዱሳን ታሪክ) ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Sinksar (Synaxarium) la Iglesia Ortodoxa Tewahedo

En el nombre del Padre, del Hijo y del Espíritu Santo, un solo Dios. ¡Amén!

Para aprender del Synaxarium o la historia y Vidas de los santos cristianos y mejorar en su cristianismo, especialmente en la vida de la Iglesia ortodoxa Tewahedo, le recomendamos que lea el libro y para aquellos de ustedes que no pudieron acceder al libro aquí. es una aplicación que contiene las historias principales con imágenes que ilustran la historia.

La mayoría de los santos son de la Iglesia Ortodoxa Oriental.

Esta comunión ortodoxa oriental está compuesta por seis iglesias autocéfalas:

- la Iglesia Ortodoxa Etíope Tewahedo,

- la Iglesia copta ortodoxa de Alejandría,

- la Iglesia Ortodoxa Siria de Antioquía,

- la Iglesia Apostólica Armenia,

- la Iglesia ortodoxa eritrea de Tewahedo, y

- la Iglesia Ortodoxa Siria de Malankara.

- En amárico e inglés.

Sigue leyendo, discute lo que has leído con otros cristianos y sigue compartiendo la aplicación con todos los cristianos del mundo.

Novedades de Última Versión 4.8.1

Last updated on 21/03/2024

- በተጠቃሚዎች ጥያቄ መሰረት ስንክሳርን በድምፅ ማዘጋጀት ጀምረናል ይህም ጅማሮ አፕሊኬሽኑ ላይ ተካቷል
- የየወሩን ስንክሳር ወደታች የየቁኑን ደግሞ ወደ ጎን ስክሮል እያረጉ በቀላሉ ማየት እንዲችሉ ተደርጓል
- የእንግሊዘኛው ስንክሳር ተካትቷል
- የአፕሊኬሽኑ መጠን ተቀንስዋል
- ፊት ለፊት ላይ በዛሬው ቀን የሚውሉትን ቅዱሳኖች ዝርዝር ማየት እንድትችሉ ተደርጎዋል
- ካለ ኢንተርኔት እንዲሰራ ተደርጓል
- የቅዱሳን ስዕላት ከነታሪኮቻቸው
- ቅዱሳን የሚውሉበት ቀን ከነታሪኩ
- ፅሁፉን ማስተለቅ ማሳነስ ያስችላል
- ታሪኩን ሼር ማድረግ ያስችላል
- የወሩን ብቻ ለማየት ያስችላል
- The English Synaxarium is Added

Traductorio...

Información Adicional de Aplicación

Última Versión

Solicitar ስንክሳር Actualización 4.8.1

Presentado por

Trung Hiền

Requisitos

Android 4.1+

Available on

Conseguir ስንክሳር desde Google Play

Mostrar más

ስንክሳር Capturas de pantalla

Comentario Cargando...
Idiomas
Idiomas
Buscando...
Suscríbete a APKPure
Sé el primero en obtener acceso al lanzamiento anticipado, noticias y guías de los mejores juegos y aplicaciones de Android.
No, gracias
Suscribirme
¡Suscrito con éxito!
Ahora estás suscrito a APKPure.
Suscríbete a APKPure
Sé el primero en obtener acceso al lanzamiento anticipado, noticias y guías de los mejores juegos y aplicaciones de Android.
No, gracias
Suscribirme
¡Éxito!
Ya estás suscrito a nuestro boletín electrónico.